ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላትን አነጋገሩ

100
አዲስ አበባ ነሐሴ 17/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላትን በፅህፈት ቤታቸው አነጋገሩ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ የአፍሪካ የዓለም አቀፍ ጤና፣ ሰብዓዊ መብቶችና ተቋማት ንዑስ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር ክሪስ ስሚዝን እና የንዑስ ኮሚቴው አባል ሚስ ካረን ባስን በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ለውጥ፣ ልማትና ዴሞክራሲ በቅርበት እንዲደግፍ ጠይቀዋል። የኮንግረሱ አባላት ወደአገራቸው ሲመለሱ የኢትዮጵያን መልካም ስም በማስተዋወቅ ሚናቸውን እንደሚወጡ መናገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ገልጸዋል። የኮንግረስ አባላቱ አትዮጵያ ወስጥ በአጭር ጊዜ የመጣው ለውጥ እንዳይደናቀፍ የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለውን ለውጥ በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑንም እንዲሁ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም