የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላት በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና የሚቃወም መርሀ ግብር እያካሄዱ ነው

78

ህዳር 23/2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላት በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና የሚቃወም መርሀ ግብር እያካሄዱ ነው።

መርሃ ግብሩ በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄደው ጣልቃ ገብነት ''ይብቃ'' በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡

የዮኒቨርሲቲው አባላት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በማንገብ እና የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሟቸውን አሳይተዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ቅጽር ግቢ የሚከናወነው መርሀ ግብር እንደተጠናቀቀ አባላቱ በአሜሪካ ኤምባሲ በር ላይ በመገኘት ተቃውሟቸውን እንደሚያሰሙ ተገልጿል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም