ድሬዳዋ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል ለማክበር ተዘጋጅታለች

52

ድሬዳዋ ህዳር 22/2014 (ኢዜአ) 16ተኛውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል በድሬዳዋ በደመቀ መንገድ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቀቀ።

የፌዳሬሽን ምክር ቤትና የድሬዳዋ አስተዳደር በበአሉ አከባበር ላይ ዛሬ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ዘሃራ ሁመድ በሰጡት መግለጫ በአሉን በደመቀ ስነ ስርአት ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል።

"ወንድማማችነት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ዘንድሮው ህዳር 29 በሚከበረው በአል በፀና አንድነት ኢትዮጵያን ለማሻገር የሚያስችሉ ሁነቶች እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጁሀር ከድር በበኩላቸው 16ተኛው የኢትዮጵያ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ቀን በአልን ህብረ ብሔራዊነትን በሚያጸና መልኩ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል።

በበአሉ አከባበር ዝግጅትና ጠቀሜታ የተመለከቱ ጉዳዮች በጋራ መግለጫው ማብራሪያ እየተሰጠ ሲሆን ዝርዝሩን ኢዜአ በዜና ዘገባው የሚያሳውቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም