ለመዲናዋ መንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ አዳዲስ የስራ ኃላፊዎች ተሾሙ

166
አዲሰ አበባ ነሀሴ 17/2010 ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ እና ለትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አዳዲስ የስራ ኃላፊዎች ተሾሙ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት እንደገለፀው ኢንጂነር ምትኩ አስማረ የከተማው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። ኢንጂነር ሰመረ ጀላሎ የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ፣ ኢንጂነር አማረ መኮንን ደግሞ የፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሥር በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት ተሿሚዎቹ በከተማዋ በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ማነቆ የመፍታት ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም