የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

202

ህዳር 22/2014 (ኢዜአ)የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ዛሬ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡በዚህም ሁለቱ ሀገራት በወቅታዊ ጉዳዮች እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።