የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ለሠራዊቱ ስንቅ እያዘጋጀ ነው

56

አዲስ አበባ ህዳር 21/2014(ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ለአገር መከላከያ ሠራዊት የስንቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ ክፍለ ከተማው ለአገር መከላከያ ሠራዊት የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ለአብነትም በተያዘው በጀት ዓመት ግንባር ላይ እየተዋደቀ ለሚገኙት ለመከላከያ ሠራዊት አባላት 105 ሚሊየን ብር ድጋፍ መድረጉን ጠቁመዋል።

አሁን ደግሞ ክፍለ ከተማው ከባለኃብቶችና ነዋሪዎች በማስተባበር በ13 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ወጪ የስንቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በስንቅ ዝግጅቱ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ ለሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋገጠዋል።

በክፍለ ከተማው ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ እታለማሁ ደምሴ፤  "ህይወቱን  ሳይሰስት  እየተዋደቀ  ለሚገኘው  መከላከያ  ሰራዊት እየተዘጋጀ  ባለው የስንቅ  ዝግጅት  በምችለው አቅም እየተሳተፍኩ ነው" ብለዋል።

ሁላችንም ተባብረን ከሰራን ኢትዮጵያን አሸናፊ እናደርጋታለን ነው ያሉት፡፡

ሁላችንም በምንችለው አቅም ስንቅ በማዘጋጀት፤ አካባቢያችን በመጠበቅና በሌሎች መንገዶች ለሠራዊቱ እየደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክረን መቀጠል አለብን ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ የክፍለ ከተማው ነዋሪ ወይዘሮ ሃና ሰይፉ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም