የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በባህር ዳር ማካሄድ ጀመረ

56
ባህር ዳር ነሃሴ17/2010 የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/  ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ በባህርዳር ከተማ የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ አዳራሽ ማካሄድ ጀመረ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባውን ከመጀመሩ አስቀድሞ በቅርቡ ህይወታቸው ላለፈው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የብአዴን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ለነበሩት አቶ ተስፋዬ ጌታቸው የህልና ጸሎት አድርጓል። የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ደመቀ መኮንን አጃንዳውን ባስተዋወቁበት እንደገለጹት ማዕከላዊ ኮሚቴው በሁለት ቀናት ቆይታው በአራት ጉዳዮች ላይ ይመክራል። የጉበኤው መነሻ ሪፖርት ቀርቦ ከክልላዊ ሁለንተናዊ ለውጡ ጋር በማያያዝ የሚገመገም መሆኑን ገልጸዋል። የድርጅቱ የ2011 በጀት ዓመት የስራ ማስፈጸሚያ በጀት ቀርቦ የሚጸድቅ ሲሆን የድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መመሪያና ህግ ላይ ውይይት በማካሄድ እንደሚሻሻል ተመልክቷል። ማዕለከላዊ ኮሚቴው በቀጣይ በሚካሄደው ጉባኤ እቅድና የአፈጻጸም ስራዎች ላይ በሰፊው በመምከርና ውይይት በማካሄድ በቀጣይ ወደ አበላት በሚወርዱት ሃሳቦች መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የድርጅቱ 12ኛ መደበኛ ጉባኤ በቅርቡ በባህርዳር የሚካሂድ ሲሆን በተለይም ለውጡን ዳር በማድረስ በኩል በአስተሳሰብና በአመለካከት የተሟላ የአመራር ሚና ለመጫወት የሚያስችል ቁመና ይዞ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም