ቻይና ለአፍሪካ 1 ቢሊየን ዶዝ የኮቪድ ክትባት ለመስጠት ቃል ገባች

90

ህዳር 21/ 2014 /ኢዜአ/ የቻይናው ፕሬዝዳንት ለአፍሪካ 1 ቢሊየን የኮቪድ ክትባት ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

አህጉሪቱ ክትባቱን ማግኘቷ የኮቪድ ተፅዕኖን ለመቋቋም ያስችላታል ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ዤ ፒንግ ሴኔጋል ዳካር እየተካሄደ ባለው የቻይና አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት እንደተናገሩት ቻይና 600 ሚሊየን ዶዝ ክትባት በቀጥታ ለአፍሪካ የምትሰጥ ይሆናል፡፡

400 ሚሊየን ዶዝ የሚሆነው ክትባቱን ለማምረት የሚያስችሉ ኢንቨስትመንቶችን በመደገፍ የሚገኝ ይሆናልም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፤ ይህም በአፍሪካ ክትባቱን ለማምረት ያለውን ክፍተት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡

ቤጂንግ በሚሊየን የሚቆጠር በራሷ ያመረተችውን ሲኖፋርም የተሰኘውን ክትባት ቻይና ለአፍሪካ ሃገራት ስትሰጥ ቆይታለች፡፡

የቻይና አፍሪካ ኮንፍረንስ የንግድና የፀጥታ ጉዳዮች ላይም መምከሩን ነው የአፍሪካን ኒውስ ዘገባ ያመለከተው ፡፡

ቻይና የአፍሪካ ትልቅ የንግድ አጋር መሆኗን የገለፀው ዘገባው እኤአ በ2019 ብቻ 200 ቢሊየን ቀጥታ የንግድ ልውውጥ ኢንቨስትመንት መደረጉን ዳካር የሚገኘው የቻይና ኢምባሲ አሳውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም