አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በደቡብ ክልል ተጀመረ

111

አዜዶቦኦ ፤ህዳር 20/2014(ኢዜአ) አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ክልላዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በካምባታ ጣምባሮ ዞን አዜዶቦኦ ትምህርት ቤት በመካሄድ ላይ ነው።

የሙከራ ትግበራው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር  በአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት መጻሕፍት ተዘጋጅተው በተመረጡ የቅድመ አንደኛ፣አንደኛ፣መካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚካሄድ ነው።

 ክልላዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር  በካምባታ ጣምባሮ ዞን ቀድዳ ጋሜላ ወረዳ አዜዶቦኦ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው እየተካሄደ ያለው።

ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ እየተሳተፉ ነው።

በዚህም ስለአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ገለጻና ማብራሪያ የሚደረግ  ሲሆን የተሰናዱ የመማሪያ ክፍሎችና መጻህፍት ምልከታ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም