የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለሚያደርገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ድጋፋችንን እንገልጻለን

72

ህዳር 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) “የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለሚያደርገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ድጋፋችንን እንገልጻለን” ሲሉ የሶማሌላንድ ኘሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድን ተቀብለው በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል።በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር በማሳደግ የጋራ ብልጽግና ማረጋገጥ በሚሉ አጀንዳዎች ላይም መምከራቸው ተገልጿል።

በዚህ ወቅት አቶ ሙስጠፌ የቀጠናው የሠላም ሁኔታን በተመለከተ ከጎሮቤት ሶማሌላንድ ጋራ ስለሚከናወኑ ጉዳዮች አብራርተዋል።የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጋራ በመከላከል በአፍሪካ ቀንድ ያሉት ህዝቦች እጣ ፋንታቸው የተሳሰረ በመሆኑ በራሳቸው ጉዳይ መወሰን የሚችሉት እራሳቸው ብቻ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በበኩላቸው “የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለሚያደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ድጋፋችንን እንገልጻለን” ብለዋል።

የበርበራ ወደብ በዩናይትድ አረብ ኢምሬቶች አስፈላጊውን የማስፋፊያ ግንባት ከተደረገበት ወዲህ ለኢትዮጵያ የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ፤ የሁለትዮሽ የንግድ ተስስሩን ለማሳደግ ዝግጅ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም