" ኢትዮጵያ ትጣራለች " የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ

100

ህዳር 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) 'ኢትዮጵያ ትጣራለች' የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በጎንደር ከተማ አስተዳደር አስተባባሪነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ፤ ገቢው በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው ሰራዊት እና ለተፈናቃይ ወገኖች መሆኑን ገልጸዋል።በመሆኑም በዛሬው እለት 'ኢትዮጵያ ትጣራለች' በሚል መርህ የገቢ ማሰባሰቡ ስራ መጀመሩን ጠቅሰዋል።

በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነው 50 ሚሊየን ብር ለመለገስ ቃል ገብተዋል። በተጨማሪም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 5 ሚሊዮን ብር፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 2 ነጥብ 25 ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገብተዋል።

በገቢ ማሳሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ ባለሃብቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች የተገኙ ሲሆን ግለሰቦች፣ ተቋማት እና ድርጅቶች ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።_

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም