"የኢትዮጵያ ልክ ለፈረንጆቹ አልተገለጸላቸውም" አባት አርበኞች

201

አዲስ አበባ ህዳር 17/2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ልክ ለፈረንጆቹ አልተገለፀላቸውም፤ ልኳ ስውር ነው የሚሉት ለእናት አገራቸው በጦር ሜዳ ተዋድቀው ጀብድ በመፈጸማቸው ዛሬም ኩራት የሚሰማቸው አባት አርበኞች ናቸው።

እነዚህ አባት አርበኞች ሰሞነኛውን የኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክተው ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸው የሰሞኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ወደ ጦር ግንባር መዝመት ያነሱት አባት አርበኞቹ ወጣቱ ትውልድ ሊከተለው የሚገባ ታላቅ አርዓያ የሚሆን ተግባር ፈፅመዋል ነው ያሉት። 

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ግንባር መዝመት ከማንም በፊት ለአገራቸው ያላቸውን ፍቅር እና እውነተኛ መሪ ለመሆናቸው ማሳያ ነው ብለውታል። ይህ ተግባራቸው ኢትዮጵያዊያንን ብቻም አይደለም አፍሪካዊያን ጭምር ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙ ያደረገ መሆኑንም አውስተዋል። 

በመሆኑም ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል መሪውን በመከተል ለአገሩ ሉዓላዊነት መከበር ወደ ግንባር በማቅናት ታሪክ የማይረሳው ጀብድ መፈጸም እንዳለበት አስገንዝበዋል።

" አባት አርበኛ ለገሰ ዳባ፡- "እናት አገሬ፤ ለአገሬ ህይወቴን እሰጣለሁ፣ እሰዋለሁ፣ እኔ እያለሁ ጁንታዎች አገራችን አይገቡም፣ አይመጣም በሚል በእውነተኛ ጀግንነት፣ እሰዋለሁ።

 አባት አርበኛ አስማማው መከተ "ኢትዮጵያ እኔ እያለሁ አትነካም፤ ኢትዮጵያ እኛ እያለን አትደፈርም በማለት የተነሳ ነው፡፡ ፈረንጆቹ ይህን አያውቁትም፡፡ የኢትዮጵያ ልክ ስውር ነው ለእነሱ፡፡ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም