የግል ትምህርት ቤቶችና የሥልጠና ተቋማት ለአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ

63

አዲስ አበባ ህዳር 14/2014 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶችና የሥልጠና ተቋማት ለአገር መከላከያ ሠራዊት ከ5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረጉ።
የትምህርት ተቋማቱ ለሠራዊቱ ያሰባሰቡትን የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የትምህርትና ሥልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሕይወት ጉግሳ ተቋማቱ ለመከላከያ ሠራዊት 4 ሚሊዮን ብር ገንዘብ እና 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊና የድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ነጂባ አክመል የግል ትምህርት ቤቶቹ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ወደ ግንባር መዝመት የሚችል ሃይል እንዲዘምት፤ በሥራ ላይ የሚቀሩም ሥራቸውን በእግባቡ በመከወን ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

 ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን የሕልውና አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ አንድነቱን ማጠናከርና ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መቆም እንዳለበትም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም