የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛው ስብሰባውን ቀጥሏል

53
አዲስ አበባ ነሐሴ 15/2010 የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛው ስብሰባውን የአመለካከት አንድነትን በሚያረጋግጥና የአመራሩን አቅም በሚገነባ መልኩ ማካሄድ መቀጠሉን አስታወቀ። መደበኛ ስብሰባውን ትናንት ማካሄድ የጀመረው የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በጥልቅ ተሃድሶው የተላለፉ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አፈፃፀም እንዲሁም ውሳኔውን ተከትሎ የመጡ ለውጦችን በጥልቀት እየገመገመ ይገኛል። ጥልቅ ተሃድሶውን ተከትሎ እየመጡ ያሉ ሀገራዊ ለውጦች የሕዝቡን ፍላጎት በሚያሟላና ምልዓት ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ እየተፈፀሙ መሆናቸውን ማየቱን የኢሕአዴግ የሕዝብና ውጪ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ ለኢዜአ ገልጸዋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ይህን ሀገራዊ ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል የአመለካከት አንድነት በድርጅቱ ውስጥ ሊያረጋግጥ በሚችልና የአመራሩን አቅም በሚገነባ መልኩ ውይይቱን እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም