በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የሕልውና አደጋ ለመመከት አመራሩ ከፊት ተሰልፎ ሚናውን ይወጣል

88

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13/2014 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የሕልውና አደጋ ለመመከት አመራሩ ከፊት ተሰልፎ ሚናውን እንደሚወጣ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ገለጸ።

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱም የኢትዮጵያን ሕልውና የማይፈልጉ የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ሃይሎች በመቀናጀት በኢትዮጵያ ላይ ሁሉን አቀፍ የሕልውና አደጋ ደቅነዋል ብሏል።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ኢትዮጵያ በታሪኳ ጠንካራ ፈተና እየተጋፈጠች መሆኗን ጠቅሶ፤ በዚሀም ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን ለመታደግ በአንድነት ቆመው አኩሪ ተጋድሎ እየፈፀሙ ነው ብሏል።

በመሆኑም ይህን የአገር ሕልውና አደጋ በመመከት የኢትዮጵያን ክብርና ሉአላዊነት ለማስከበር አመራሩ ከፊት ተሰልፎ ሚናውን እንደሚወጣ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም