የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምስረታ በነገው እለት ይካሄዳል

86

ህዳር 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምስረታ በነገው እለት በቦንጋ ከተማ ይካሄዳል፡፡

መርሃ ግብሩ የሚካሄድባት የቦንጋ ከተማ እንግዶቿን ለመቀበል ከወዲሁ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡

የቦንጋ ከተማ ጎዳናዎች በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ደምቀዋል፤ የከተማዋ ነዋሪዎችም እንግዶቻቸውን በደማቅ ሁኔታ ለመቀበል ተዘጋጅተዋል፡፡

በነገው መርሃ ግብር የክልል ምስረታ፣ የክልሉን ህገ-መንግስት ማጽደቅ፣ አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባኤ መምረጥ፣ ርዕሰ- መስተዳድር መምረጥ እንዲሁም የተለያዩ አዋጆችን የማጽደቅ ተግባር ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ማስተዋወቅም በነገው ዕለት ከሚካሄዱ መርሃ-ግብሮች መካከል ይገኝበታል።

በምዕራብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ፣ ካፋ፣ ዳውሮና ሸካ ዞኖች እንዲሁም በኮንታ ልዩ ወረዳ  የሚኖሩ ህዝቦች መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ሕዝበ-ውሳኔ በማካሄድ ክልል ሆነው የመደራጀት ይሁንታ ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል በነገው እለት የሚመሰረት ሲሆን፤ በመርሃ ግብሩም የፌዴራልና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም