የሐረሪ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ጣልቃገብነትን በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል

87

ሐረር ፤ ህዳር 13/2014(ኢዜአ) የሐረሪ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ጣልቃገብነትን በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል ።

ሰራተኞቹ  “NO MORE” “በቃ” በሚል  መሪ ሀሳብ አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ የምዕራብያውያን ሀገራትና የመገናኛ ብዙሃኖቻቸው በኢትዮዽያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና በአንድነት እያወገዙ ነው።

ምዕራብውያኑ  በኢትዮዽያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የሚያካሂዱት ጫና እንዲበቃ እና  መገናኛ ብዙሃኖቻቸው  እውነተኛውን ዘገባ  እንዲያቀርቡም እየጠየቁ ይገኛሉ።

በመረሃ ግብሩ ላይ የሐረሪ  ክልል  ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ፣የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ   ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልጀባር መሃመድ ጨምሮ ሌሎችም  ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የሴክተር መስሪያ ቤት ሰራተኞች እየተሳተፉ መሆናቸውን የኢዜአ ሪፖርተር ከሐረር ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም