የአሜሪካ መንግስትና ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና የሚቃወም ሰልፍ በለንደን እየተካሄደ ነው

128

ህዳር 12/2014 (ኢዜአ) የአሜሪካ መንግስትና አንዳንድ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና የሚቃወም ሰልፍ በለንዴን እየተካሄደ ነው።

አሸባሪው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በግልፅ እየተንቀሳቀሰና እጂግ ጭካኔ የተሚላበት ወንጀል እየፈፀመ ባለበት በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ መንግስትና አንዳንድ ምእራባዊያን አገራት በመንግስት ላይ ያልተገባ ጫና በማድረስ ላይ ይገኛሉ።

የአሜሪካኑን የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲ ኤን ኤን ጨምሮ ቢቢሲ፣ አልጀዚራ እንዲሁም ሌሎች የውጭ ሚዲያዎች ከአሸባሪው ህወሃት ወግነው የፈጠራ ወሬና የሃሰት መረጃ በማሰራጨት ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

May be an image of 6 people and people standing

በመሆኑም እነዚህን ድርጊቶች የሚቃወም ሰልፍ  በእንግሊዝ ለንደን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የሰልፉ ዋነኛ ዓላማ የአሜሪካና አጋሮቿን ያልተገባ ጣልቃ ገብነትና ጫና መቃወም እንዲሁም የሀሰት መረጃ እያሰራጩ ያሉ ሚዲያዎቻቸው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የሚጠይቅ መሆኑን በለንደን የሚኖሩት የሰልፉ ታዳሚ አቶ አለባቸው ደሳለኝ በተለይም ለኢዜአ ገልጸዋል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ በለንደን የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን የተለያዩ መልእከቶችን አንግበው ወደ እንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እያመሩ መሆኑን አሳውቀውናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም