ለሕልውና ዘመቻው ስኬት ሁለንተናዊ ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል

87

ህዳር 10/2014 (ኢዜአ) የሕልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ የጋምቤላ ክልል ሕዝብና መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ተወያይተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የሕልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍን አጠናክሮ ይቀጥላል።

የህወሓት የሽብር ቡድን በከፈተው ጦርነት ለተፈናቁሉ ወገኖችና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚደረገው  ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የሽብር ቡድኖቹ በሀገር ላይ የደቀኑትን ፈተና ለመቀልበስ በሚደረገው ጥረት የክልሉ ህዝብና መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍን አጠናክሮ ይቀጥላል።

በህወሓት የሽብር ቡድንና ተላላኪዎች በከፈቱት ጦርነት የተፈናቀሎ ወገኖችን ጨምሮ በግንባር ለሚፋለመው የጸጥታ ኃይል የክልሉ ህዝብና መንግስት ድጋፍና ደጀንነት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

የሽብር ቡድኖቹ በተለይም በአፋርና በአማራ ክልል በከፈቱት ጦርነት የተፋናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ የክልሉ መንግሥት 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለመስጠት መወሰኑን ገልጸዋል።

የክልሉን የንግድ ማህበረሰብ በማስተባበር ተጨማሪ ድጋፍ እየተሰባሰበ መሆኑን ተናግረዋል።

የህወሓት የሽብር ቡድን የከፈተውን ጦርነት ህዝቡን በማስተባበር በአጭር ጊዜ  ለመቋጨት እየተደረገ ላለው ጥረት የክልሉ ህዝብና መንግስት ከኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር እየተረባረበ ነው።

ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ባህሩ ሸሪፋ እንዳሉት የተፈናቀሉ ወገኖችን ከመደገፍ ጀምሮ በሀገር ላይ የተቀጣውን ወቅታዊ የሕልውና አደጋ ለመቀልበስ አስፈላጊውን መሰዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ብለዋል።

ሌለው ተሳታፊ አቶ አህመድ አሸናፊ እንሉት ከአሁን በፊት 10 ሺህ ብር ድጋፍ መስጠታቸውንና በቀጣይም የተቻለቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ናቸው።

በውይይቱ በድረኩ ላይ 150 የሚሆኑ የንግድ ማህበረሰብ የተገኙ ሲሆን በዕለቱም ከ357 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተሰባስቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም