"ዳጉ" የህወሓት የሀሰት ፕሮፓጋንዳን ከመመከት አልፎ የጠላትን እንቅስቃሴ በማክሸፍ የጎላ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው

68

ሰመራ፣ ህዳር 09 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአፋር ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት "ዳጉ" የህወሓት የሀሰት ፕሮፓጋንዳን ከመመከት አልፎ የጠላትን እንቅስቃሴ በማክሸፍ የጎላ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ።

የህወሓት ሽብር ቡድን ፍላጎታቸውን ለማሳካት በሀገር ላይ እየፈጸሙ ለሚለገኘው ክህደት የትግራይ ህዝብ መጠቀሚያ መሆኑ አይገባውም።

የማዕድን ሚኒስቴር በጦርነቱ ለተጎዱ ተቋሞች መልሶ ግንባታ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ዛሬ አበርክቷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ አሸባሪው ህወሓት 'ታላቋን ትግራይ ለመመስረት ኢትዮጵያን ማፍረስ አለብኝ' ብሎ ያለ የለሌ ኃይሉን አሟጦ የግፍ ጦርነት አውጆብናል።

በአፋር ግንባር አሸባሪው ህወሓት በዋናነት የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ መስመርን በመቆጣጠር እንደመደራደሪያ ለመጠቀም አልሞ ያለውን አቅም ሁሉ አሟጦ እየሞከረ ነው።

የአፋር ህዝብ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን በቅንጅት የሽብር ቡድኑን የጥፋት ህልም ቅዠት ሆኖ እንዲቀር እያደረጉት ይገኛሉ ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት፤ በተለይም የጥፋት ቡድኑ ሚሌን ለመቆጣጠር አልሞ በከፈተው ጦርነት በመከላከያ ሠራዊታችን እየደረሰበት ባለው ጠንካራ ምት ተሽመድምዶ እየተፍረከረከ ይገኛል።

በዚህ ግንባር ህዝቡና ሠራዊቱ የፈጠሩት ጠንካራ ቅንጅትና መናበብ ጠላት መከላከያ ሰራዊቱን ፊት ለፊት ከመጋፈጥ ይልቅ በየጢሻው ተሽሎክሉኮ ለማምለጥ ቢሞክርም አርብቶ አደሩ ህዝብ እያሳደደ መግቢያ መውጫ እያሳጣው ነው።

የሽብር ቡድኑ በጦር ግንባር የደረሰበትን ኪሳራ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ለማደናገር የተለያዩ የውዥንብር መረጃዎችን ለመልቀቅ ቢሞክርም ዳጉን የመሠለ የጠራ አስተማማኝ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ባለቤት የሆነው የአፋር ህዝብ ለዚህ ቦታ እንደለሌው በተግባር አሳይቷል ብለዋል።

የዳጉ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት ባለቤት የሆነው የአፋር አርብቶ አደር በጦርነቱ ተደናግጦ ከቤቱ ከመሸሽ ይልቅ በአካባቢው ተረጋግቶ እራሱን እየተከላከለ የጠላትን እንቅስቃሴና ተያያዥ መረጃዎችን ለወገን ጦር ፈጥኖ በማድረስ ጠንካራ ህዝባዊ ደጀንነቱን አስመስክሯል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንደዚህ አይነት የህዝብ ድጋፍ ካለው ለአሸባሪው ህወሃት ብቻ ሳይሆን ለውጭ ወራሪዎችም የማይመለስ፤ የማይገፋ ተራራ መሆኑን በአፋር ግንባር ተጋድሎ የሠራዊቱን አኩሪ ገድል በተግባር አይተናል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ።

አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈጸመው ጥቃት መጥፎ የማይሽር ጠባሳ እንደተወም ገልጸዋል።

"የሽብር ቡድኑ የጥፋት ዓላማውን ለማሳካት አቅመ-ደካማና ሕጻናትን ጨምሮ የትግራይ ህዝብን በገፍ እንደቅጠል እያረገፈ ይገኛል" ብለዋል።

በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገለል በማድረግ የጥፋት ቡድኑ ፍላጎት ማስፈጸሚያ መሳሪያ እያደረገው በመሆኑ ከማንም በላይ የትግራይ ህዝብ ቆም ብሎ ቡድኑን በቃህ ሊለው ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም