የምእራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ሃገራት (ኢኮዋስ ) የወባና የኮቪድ 19 ክትባትን ሊያመርቱ ነው

123

ህዳር 6/2014 የምእራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ሃገራት (ኢኮዋስ ) አስራ አምስት አባል ሃገራት የወባና የኮቪድ 19 ክትባቶችን በሴኔጋል፣በናይጄሪያና በጋና ለማምረት ማቀዳቸው ታውቋል ፡፡

አናዶሉ ሌጎስ የሚታተመውን ጋርዲያን ጋዜጣ ጠቅሶ እንደዘገበው የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃመድ ቡሃሪ ለአባል ሃገራቱ  እንዳሳሰቡት  የወባና የኮቪድ ክትባቶች  በራስ አቅም ቢመረቱ በአፍሪካ ያለውን የክትባት ፍትሃዊነት ችግር ለመቅረፍ ያስችላሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ቡሃሪ የኢኮዋስ አባል ሃገራት የኮቪድ 19 የለውጥ ሂደት ለማጥናት በአንድነትና መፍትሄ ሰጪ በሆነ መልኩ መስራት እንዳለባቸው ገልፀው  አፍሪካ በሚሰሩ አዳዲስ  ምርምሮችና ውጤቶቻቸው ላይ ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል በተለይም  የአንድን ነገር መነሻ መለየት የሚያስችሉ የላብራቶሪ ጥናቶችና ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኖችን በሃገር አቀፍና በአህጉር ደረጃ እንዲሁም የህብረተሰብ የጤና ስጋቶች ን ሊያጠኑ ይገባል፡፡

በጥቅሉ በወባ መሞት በአፍሪካና በምእራብ አፍሪካ መቀነስ ቢያሳይም አሁንም በናይጄሪያ  በቦርኪናፋሶ፣በኒጀር፣በማሊ፣በአይቮሪኮስት ፣በጋና እና ጊኒ የሞት ምጣኔው ከፍተኛ ነው ፤ይህም  ወባን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረት ጥያቄ የሚያስነሳ ነው  ብሏል መረጃ ው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ባለፈው መስከረም ባወጣው መረጃ በአፍሪካ አምስት ሃገራት ብቻ በእቅድ የተያዘውን ከዜጎቻቸው  40 ከመቶ የኮቪድ 19 ክትባት  ማድረስ የቻሉት፤አፍሪካ አሁንም ክትባቱን ለማድረስ መሰረታዊ የሆኑ ስሪንጅን የመሳሰሉ የህክምና መሳሪያዎችን ለማሟላት ትግል ላይ ነች፡፡

የተባበሩት መንግስታት 143 ሚሊየን የኮቪድ 19 ክትባት ለአፍሪካ እንዲደርስ ያደረገ ሲሆን 39 ሚሊየን  ሰዎች አልያም 3 ከመቶ  ተከትበዋል ፤ በአሜሪካ  52 ከመቶ  በአውሮፓ ህብረት 57 ከመቶ ክትባቱ መዳረሱን ዘገባው አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም