የአራዳ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሠራዊት ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አሰባሰበ

96

ህዳር 05 2014 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ የአራዳ ክፍለ ከተማ ለአገር መከላከያ ሠራዊት  ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ በስምንት ቀናት  ማሰባሰቡን ገለጸ።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አባወይ ዮሃንስ፤ ህብረተሰቡ መከላከያ ሰራዊቱን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ  በመደገፍ ደጀንነቱን በተግባር ማሳየቱን ቀጥሏል ብለዋል።

ይህም ህብረተሰቡ ሰራዊቱን በመደገፍና በሌሎችም ተግባራት እያሳየ ያለው ተነሳሽነትና አንድነት የሚያመላክት ሲሆን የዜግነት ድርሻውን ለመወጣት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

"እንደ ክፍለ ከተማችን በ8 ቀን ውስጥ ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብት ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ማሰባሰብ ችለናል" ነው ያሉት።

ከዚህ ጎን ለጎን የአካባቢው ማህበረሰብ በበጎ ፈቃደኝነት የስንቅ ዝግጅት በሁሉም ወረዳዎች እያካሄድ ነው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ከድጋፉ በተጨማሪ በርካታ ወጣቶች የአገር መከላከያ ሰራዊትን እየተቀላቀሉ መሆኑን ጠቅሰው "ኢትዮጵያዊያን በመዝመት፣ ሰራዊቱን በመደገፍ፣ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ በዘመቻው ሊሳተፉ ይገባልም ብለዋል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም