በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅቱ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

35
አዲስ አበባ ነሐሴ 14/2010 የትምህርት ፖሊሲው የተሻለና አመርቂ ውጤቶች እንዲመዘገቡበት የወቅቱን ቴክኖሎጂም ግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሆን በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ላይ ማሻሻያ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡ ለ15 ዓመታት ለሚተገበረው  አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ውይይት ማድረግ ተጀምሯል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት ሲሆን በውይይቱ ላይ ከ26 ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡ ውይይቱ ለትምህርና ስልጠና ፍኖተ ካርታው ዝግጅት ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ ሲሆን በተሳታፊዎች የሚነሱ ተጨማሪ የማሻሻያ ሃሳቦች ተካተው አስፈላጊው ውይይት ተደርጎበት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ውይይቱ ለአምስት ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል፤ ዝርዝር መረጃው እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም