በሽብርተኛው የሸኔ ቡድን ላይ በተወሰደ እርምጃ 170 የቡድኑ አባላት ሲደመሰሱ 12ቱ ተማርከዋል

66

ነገሌ፣ ጥቅምት 20/2014(ኢዜአ) በጉጂ ዞን ባለፉት ሶስት ወራት በሽብርተኛው የሸኔ ቡድን ላይ በተወሰደ እርምጃ 170 የቡድኑአባላትሲደመሰሱ 12ቱ ከነሙሉትጥቃቸውመማረካቸውንየዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ቡድኑ በንጹሃን ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለማስቆም በተካሄደው እንቅስቃሴ ውጤታማ ስራ መከናወኑን የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር ብዙነህ ቦዲና ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

የአባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶችን ምክር የተቀበሉ 51 ግለሰቦች ደግሞ ለጸጥታ ሀይሉ እጃቸውን በሰላም መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

ተታለው ቡድኑን በመቀላቀል ጥቃት ለማድረስ ስልጠና ላይ የነበሩ 72 አባላቱ በሽብር ተግባር ሳይሳተፉ በቁጥጥር ማዋል ተችሏል ነው ያሉት።

በሰላም እጃቸውን የሰጡ የቡድኑ አባላት ምክር ተሰጥቷቸው ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም አደንዛዥ እጽ፣ ጫትና ተተኳሽ ጥይት የሚያቀርቡ የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው አምስት ሞተር ብስክሌቶች ፣ አንድ ፒክ አፕና አንድ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል ኮማንደር ብዙነህ ፡፡

በዚህም 6 ሺህ የክላሽንኮቭ፣ 898 የብሬን ተተኳሽ ጥይቶችና አምስት ኩንታል አደንዛዥ እጽ ከሰባት ተጠርጣሪዎች ጋር መቆጣጠር እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡

የሽብር ቡድኑን ተግባር የተቃወሙና የሰላም አማራጭን የተቀበሉ አባላትና አመራሮቹ አሁንም በየቀኑ እጃቸውን በሰላም እየሰጡ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

በቅርቡ ስምንት አባላት እጃቸውን በሰላም እንደሰጡ የሚታወስ ነው፡፡

ባለማወቅ ተታለው በንጹሀን ላይ ጥቃት ለማድረስ የሽብር ቡድኑን የተቀላቀሉ ታጣቂዎች አሁንም ወደ ሰላም የመመለስ አማራጭና እድል እንዳላቸውም ኮማንደሩ አስታውቀዋል፡፡

ኮማንደሩ እንዳሉት፤ አሁንም ርዝራዦቹን ለመቆጣጠር በዞኑ፣ በኦሮሚያና ፌደራል የጸጥታ ሀይሎች ቅንጅት የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም