የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ የጤና አመራሮች የሱማሌ ክልል የጤናው ዘርፍ እንቅስቃሴን እየገበኘ ነው

66

ጅግጅጋ፤ ጥቅምት 19/2014 (ኢዜአ) ዶክተር ሊያ ታደሰ ና ከፍተኛ የጤናው ዘርፍ አመራሮች በሱማሌ ክልል በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን እየገበኙ ነው።

አመራሩ እየጎበኛቸው ካሉት  ውስጥ በክልሉ ፋፈን ዞን የእውበሬ ወረዳ የጎቦብሌ ጤና ኬላ ይገኝበታል።

እንዲሁም ሌሎችም በክልሉ  የተለያዩ ዞኖች በሚገኙ ጤና ተቋማት የተከናወኑ ተግባራትን  በመዘዋወር እንደሚመለከት ይጠበቃል።

ቀጥሎም የጤናው ሴክተር ዓመታዊ ጉባኤ "ምላሽ ሰጪ የጤና ስርዓት በአዲስ ምዕራፍ"በሚል መሪ ሃሳብ ለ23ኛ ጊዜ በጂግጂጋ ከተማ  ይካሄዳል።

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤው ከፌደራል፣  ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጣው የዘርፉ አመራሮችና የጤና ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

በዚህም በጤና ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች የሚገመገም ሲሆን፤  ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡና የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ  የጤና ዘርፍ ባለሙያዎች እውቅና እንደሚሰጥ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም