የምዕራብ ጎጃም ዞን በአሸባሪው ህወሃት ለተፈናቅሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ አቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
የምዕራብ ጎጃም ዞን በአሸባሪው ህወሃት ለተፈናቅሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ አቀረበ
56
ጥቅምት 17/2014 (ኢዜአ) የምዕራብ ጎጃም ዞን በአሸባሪው ህወሓት ወራሪ ኃይል ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለተጠለሉ ዜጎች የሚውል 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ።
የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊና የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ወንድሜነህ ልየው ድጋፉ በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች 'አለኝታነታችንን ለማሳየት የተደረገ ነው' ብለዋል።
ያበረከቱት ድጋፍ ዱቄት፣ በቆሎ፣ አልባሳት እና ሌሎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት እንደሆነ ገልጸዋል።
በወራሪው ኃይል ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ኃላፊ አቶ መሳይ ማሩ 'ለወገን ደራሹ ወገን ነው' በሚል የምዕራብ ጎጃም ዞን ላደረገው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።