ማህበሩ በወሎ ግንባር እየተፋለሙ ለሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ከ300 ሺህ ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ አደረገ

62

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአማራ የህግ ባለሙያዎች ማህበር አሸባሪው ህወሃትን ለመደምሰስ በወሎ ግንባር እየተፋለሙ ለሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ከ300 ሺ ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አድርጓል።

በማህበሩ የተደረገው ድጋፍ ወራሪው አሸባሪ ህወሃትን ለመደምሰስ የሞራል ስንቅ ይሆናልም ተብሏል።

ድጋፉ "ራስን መከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው" በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተደረገው።

የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አያሌው፥ ድጋፎቹ ጫማ፣ የምግብ ማብሰያ እና ሩዝ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

አጠቃላይ ከ300 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው መሆኑን ጠቁመው፤ ቀጣይም አቅማቸው የፈቀደውን ድጋፋ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

የተደረገው ድጋፍ ወራሪውን የህወሓት ኃይል ለማጥፋት የሞራል ስንቅ እንደሚሆን ተናግሯል።

ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እያደረገ ያለውን የደጀንነት ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርቧል።

ወጣቱም ወራሪውን አሸባሪ ሃይል ለማጥፋት በሚደረገው ተጋድሎ ፈጥኖ መሳተፍ እንዳለበት አስገንዝቧል።

አሸባሪው ህወሃት በአማራና አፋር ክልሎች የፈጸመውን ወረራ የአገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች እየመከቱት ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም