የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በጎ ሚና ለማጉላት በኃላፊነት ስሜት መጠቀም ይገባል

51

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13/2014 ( ኢዜአ) የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በጎ ሚና ጎልቶ እንዲወጣ በኃላፊነት ስሜት መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው 14ኛው ዙር "ጉሚ በለል" የማኅበራዊ አንቂዎች ሚና በልማትና በአፋጣኝ ማኅበራዊ መፍትሄዎች በሚል ርዕስ እየተካሄደ ባለው ውይይት ነው።

የውይይት መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት የዌዱ ኢንተርቴይመንት እና ኢቨንት ምክትል ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አመሱ ቀና የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ የራሱ አበርክቶ እንደነበረው ገልጸዋል።

የማኅበራዊ  መገናኛ አማራጮች ያላቸው በጎ ሚና ጎልቶ እንዲወጣ በስነ-ምግባርና ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ መጠቀም እንደሚገባም አመልክተዋል።

ማኀበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በኃላፊነት ስሜት አለመጠቀም አሉታዊ ጉዳቱ የከፋ ነው ያሉት ወይዘሮ አመሱ በአጠቃቀም ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በቀረበው የውይይት መነሻ ጽሁፍ ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

"ጉሚ በለል" በ2013 ዓ.ም መጀመሪያ በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አማካኝነት የተጀመረ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሚካሄድ የውይይት መድረክ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም