የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 13 የካቢኔ አባላት ሹመት አጸደቀ

93

ሐረር፤ ጥቅምት 12/ 2014(ኢዜአ) አዲሱ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባዔ የቀረቡለትን 13 የካቢኔ አባላትን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቀቀ።

ምክር ቤቱ ሹመቱን ያጸደቀው  የክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በድጋሚ እንዲያገለግሉ የመረጣቸው አቶ ኦርዲን በድሪ ባቀረቧቸው የካቢኔ አባላት ላይ አስተያየት እና ድምጽ ከሰጠ በኋላ ነው።

በዚህም፡-

1/ ወይዘሮ ሚስራ አብደላን የሐረሪ ክልል ምክትል  ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ

2/ አቶ በቀለ ተመስገን የገቢዎች ቢሮ ሀላፊ

3/አቶ ተውለዳ አብዶሽ የባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

4/አቶ ሙክታር ሳሊህ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ

5/ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ

6/ዶክተር ኢብሳ ሙሳ የጤና ቢሮ ሀላፊ

7/ወይዘሮ ፈሪሀ አቡበከር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ

8/ወይዘሮ ደሊላ ዩሱፍ የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ

9/ወይዘሮ ጠቢባ አብደላ የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ

10/ አቶ እስማኤል ዩሱፍ የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሀላፊ

11/ አቶ አዩብ አህመድ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

12/ ወይዘሮ ሰሚራ ዩሱፍ  የአንተርፕራይዞች ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ እና

13/ አቶ ጥላሁን ወደራ ጎበና የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ በመሆን ተሸመዋል።

ተሿሚዎቹም  በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ከፈጸሙ በኋለ የመስራች ጉባዔው መረሃ ግብር ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም