በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደር ጅማ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ

72

ጅማ ፤ ጥቅምት 11/2014 (ኢዜአ) የኢንዶኔዥያ አምባሳደር አል ቡሲራ ባስኑር ከኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ሉኡክ ጋር በመሆን የጅማ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ።

የጉብኝቱ ዓላማ በጅማ ዩኒቨርሲቲና በኢንዶኔዥያ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የትምህርት ትስስር ለመፍጠር እንደሆነም አምባሰደሩ ተናግረዋል።

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መሆኑን ያወሱት አምባሳደሩ፤ የኢንዶኔዥያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደፊት አብረው በመሥራት ደስተኛና ውጤታማ ይሆናሉ ብለዋል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር  ጀማል አባፊጣ በበኩላቸው፤  ዩኒቨርሲቲው ከውጭ ሀገር ተቋማት ጋር ለመስራት ብዙ ዕቅዶች እንዳሉት ተናግረዋል።

የኢንዶኔዥያ አምባሳደር አልቡሽርያ ባስኑር  ከኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ሉኡክ ጋር ጉብኝት ያደረጉት የዩኒቨርሲቲውን የግብርና ኮሌጅ የኤላ ዳሌ እርሻ ምርምር ማዕከልን፣ በጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት የሕክምና ማዕከላትና የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ነው።

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ሳምንታት ከአሜሪካው የቴክሳስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና ከኤሚሬቱ ፋቲማ የጤና ኮሌጅ ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት መፈረሙም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም