በኔፓል እና በሕንድ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከ160 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ

104

ጥቅምት 11/2014 (ኢዜአ) በህንድ ኡትራካንድ እና ከራላ በተባሉ ግዛቶች እና በኔፓል የጣለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ጎርፍ 166 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡

አደጋው በርካታ መኖርያ ቤቶች በመሬት መንሸራተት ምክንያት መውደማቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡በህንድ ኡትራካንድ ግዛት ቢያንስ 50 ሰዎች እንዲሁም በኔፓል 77 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በሁለቱም አገሮች ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች የገቡበት አይታወቅም ተብሏል፡፡

በሕንድ ኬራላ ግዛት ደቡባዊ ክፍል በጣለው ዝናብ በደረሰው የጎርፍ አደጋም 39 ሰዎች መሞታቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡የጎርፍ አደጋውን ተከትሎ በግዛቱ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጨምሮ የሌሎች ተቋማት የስራ እንቅስቃሴ መስተጓጎሉ ተነግሯል።

በያዝነው ወር የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ከፍተኛ የዝናብ መጠን በእነዚህ ሀገራት ውስጥ መመዝገቡ ታውቋል።የህንድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት የዝናብ መጠኑ በቀጣይ ሳምንታት እየቀነሰ እንደሚመጣ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጎረቤት የሆነችው ቻይናም በተመሳሳይ ሰሞኑን የደረሰው የጎርፍ አደጋ በርካታ ዜጎችን ለሞት እና ከመኖርያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ማድረጉን መግለጿ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም