የትምህርት ፖሊሲው በርካታ ጥቅሞችን ያስገኘ ቢሆንም አተገባበሩ ላይ ችግሮች እንዳሉበት ተለይቷል-ዶክተር ጥላዬ ጌቴ

71
አዲስ አበባ ነሃሴ 12/2010 በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የትምህርት ፖሊሲ በርካታ ጥቅሞችን ያስገኘ ቢሆንም አተገባበሩ ላይ ችግሮች እንዳሉበት መለየቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ዘርፉ አለበት የሚባሉትን ችግሮች የለየ ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት ባለፉት ሁለት አመታት ጥናት ሲደረግ መቆየቱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ሚኒሰትሩ ዶክተር ጥላዩ ጌቴ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሀገሪቷ ላለፉት 24 ዓመታት ሲሰራበት የቆየው የትምህርት ፖሊሲ ያስገኛቸው ጥቅሞች ቢኖሩም ፖሊሲውን በመተግበር ረገድ ችግሮች እንዳሉት ተለይቷል። ይሄው ፖሊሲ ዜጎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲሔዱ፣ በመካከለኛና በመለስተኛ ዘርፍ የሰለጠኑ ምሩቃን እንዲበዙ፣ የግብርናና ጤና ኤክስቴንሽን መስኮችን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የሰው ኃይል እንዲበራከቱ ከፍተኛ አሰተዋጽኦ አበርክቷል ነው የተባለው። በፖሊሲው አተገባበርና በትምህርት ጥራት ረገድ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣትም በስፋት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ሚኒስትሩ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም