ከሳዑዲ አረቢያ 324 ዜጎች ወደ አገር ተመለሱ

48

ጥቅምት 8/2014 (ኢዜአ) በሳዑዲ አረቢያ ፣ጂዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 324 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ ወደ አገር መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም