428 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገር ተመለሱ

77

ጥቅምት 6/2014 (ኢዜአ) ከሳዑዲ አረቢያ 428 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት ከሳዑዲ አረቢያ፣ ሪያድ 172 ህጻናትን ጨምሮ 428 ዜጎች ዜጎች በትናንትናው ዕለት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም