በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ስራዎችን እየጎበኘ ነው

64

ጥቅምት 06 ቀን 2014 (ኢዜአ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ስራዎችን እየጎበኘ ነው።

በጉብኝቱ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የልዑኩ አባላት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው ደንካካ ቀበሌ የጤፍ ሰብል ክላስተር እየጎበኙ ሲሆን፤ ጉብኝቱ ዛሬና ነገ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

ከሰሞኑ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የግብርና ስራዎችን መጎብኘቱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም