ራዕይ ህዝባዊ ንቅናቄ ወደ ራዕይ ፓርቲነት አደገ

91

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) ራዕይ ህዝባዊ ንቅናቄ ወደ ፓርቲነት ማደጉን የንቅናቄው መስራችና የፓረቲው ሊቀ መንበር አቶ ሊላይ ሀይለማርያም አስታወቁ።

ከዚህ ቀደም"ራዕይ ህዝባዊ ንቅናቄ" በመባል ሲጠራ የነበረው ንቅናቄ ወደ ራዕይ ፓርቲነት መቀየሩን አስታወቀ።

የንቅናቄው መስራች እና የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ሊላይ ሀይለማርያም በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ንቅናቄው ወደ ፓርቲነት ለመቀየር የወሰነው ከአገር ውስጥም ከውጭ የትግራይ ተወላጆች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው።

በአሁኑ ወቅት ፓርቲው ጠንካራ ህዝባዊ ድጋፍ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።

የፓርቲው መቋቋም አሸባሪው ህወሀት ትግራይ ህዝብን ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖ  ለማክሸፍ ትልቁን ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

ፖርቲው በዋናነት በሰባት ዋና ዋና አምዶች ላይ ተመርኩዞ እንደሚሠራም ገልጸዋል።

ቡድኑ በባህሪው ሰላም የማያውቅ አመራር አባላት ስብስብ መሆኑንም ገልጸዋል።

መንግስት ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያደረገው ጥረት ያነሱት የፓርቲው ሊቀመንበር፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ችግሩን ለመፍታት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካም ገልጸዋል።

ቡድኑ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማታለል ስለ ሰላም እንደሚያወራ ገልጸው፤ ይህ ግን "ፈጽሞ ከባህሪያቸው ጋር የማይገናኝ ነው" ብለዋል።

አሸባሪው "ህወሀት ወደሰላም ይመጣል ብሎ ማሰብ መዘናጋት ብቻ ነው" ሲሉም ጠቁመዋል።

አሸባሪው ሕወሓትን መላው ኢትዮጵያዊ ከመንግስት ጎን በመቆም ሊፋለመው እንደሚገባም ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም