የኢትዮጵያንና የባንግላዴሽን የኢንቨስትመንት ግንኙነት የሚያጠናክር ምክክር ተካሄደ

44

ጥቅምት 4 / 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያንና የባንግላዴሽን የኢንቨስትመንት ግንኙነት የሚያጠናክር እና በኢትዮጵያ ያለውን የዘርፉን አማራጭ የተመለከተ ምክክር ተካሄደ።የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ የባንግላዲሽ አምባሳደር ከሆኑት ናዝሩል ኢስላም ጋር በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የሁለቱን ሀገራት የኢንቨስትመንት ግንኙነትን ማጠናከር፣ የባንግላዲሽ ኢንቨስተሮች ሊሳተፉባቸው የሚችሉበት የኢንቨስትመንት እድል እና አማራጮች የተመለከቱ ሃሳቦች በውይይቱ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።

የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች በጋራ የማስተዋወቅ ተግባርም በውይይቱ በአንኳርነት ከተነሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም