እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአፋር ሕዝብ ዛሬም ለሰንደቅ ዓላማው ክብር ዋጋ እየከፈለ ነው

65

ሰመራ ፤ጥቅምት 1/2014 (ኢዜአ) እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአፋር ሕዝብ ዛሬም ለሰንደቅ ዓላማው ክብርና ለሀገሩ ሉዓላዊነት ዋጋ እየከፈለ መሆኑን የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ አሰያ ከማል አስታወቁ።

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰመራ ከተማ  ተከብሯል።

አፈ ጉባዔዋ በወቅቱ  እንደተናገሩት ፤ የክልሉ ሕዝብ ለሰንደቅ ዓላማውና ለሀገሩ ባለው ፍቅር ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሳውን የአሸባሪውን ህወሓት ጥቃት ለማክሸፍ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው።

የክልሉ ሕዝብ  አሸባሪው ቡድን የሀገሪቱን ዋነኛ የገቢና ወጪ ንግድ መሥመር ለመዝጋት የነበረውን ዕቅድ ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን ተሰልፎ በመፋለም ድባቅ በመምታት ማክሸፉን ገልጸዋል።

ሕዝቡ ለሀገሩ ሉአላዊነትና ለሰንደቅ ዓላማው ክብርም ማናቸውንም ዋጋ ለመክፈል እንደቀድሞ ሁሉ ዛሬም ቁርጠኛና ዝግጁ መሆኑን አፈ-ጉባኤዋ አረጋግጠዋል።

እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአፋር ህዝብ  የማንነት መገለጫቸው የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ በማስከበር የሀገሪቱ ሉአላዊነት ለማስቀጠል ታሪካዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።


የአፋር የሃይማኖት መሪ ሱልጣን ዓሊ ሚራህ በአንድ ወቅት "ሰንደቅ ዓላማችንንና የሀገራችንን ዳርድንበር እንኳን እኛ ግመሎቻችንንም ጠንቅቀው ያውቃሉ" ያሉትን ታሪካዊ ንግግር የጠቀሱት ወይዘሮ አሰያ፤ የአሁኑም ትውልድ በተግባር ኢትዮጵያዊነቱንና ለሰንደቅ ዓላማው ያለውን ፍቅር አረጋግጧል ብለዋል።

በበዓሉ ላይ ሰንደቅ ዓላማ የመሰቀል ሥነሥርዓት ተካሄዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም