በባኮ ቲቤ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ቡና ተያዘ

103
አምቦ ነሀሴ 11/2010 በምዕራብ ሸዋ ዞን  ባኮ ቲቤ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ከ332 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው የቡና ምርት መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ቡናው የተያዘው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-32655 አ.አ. በሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ከምስራቅ ወለጋ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እንዳለ ትናንት ሌሊት አምስት ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል በወረዳው ደንቢ ዲማ ቀበሌ በተሽከርካሪው ላይ ድንገተኛ ፍተሻ  በማካሄድ 32 ኩንታል የሆነው  የቡና ምርቱ ሊይዝ ችሏል፡፡ የባኮ ቲቤ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ጽህፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ምክትል ሳጅን ረቡማ ጉዲና ለኢዜአ  እንዳሉት ህጋዊ ሰነድ የሌለውና ቅቤ አስመስሎ ለማሳለፍ የተሞከረው ይሄው ቡና በኤግዚቢትነት በጣቢያው ይገኛል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አሽከርካሪውና ሌላ አንድ ግለሰብ ተይዘውም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም