አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 556 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 556 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው
85
አርባ ምንጭ ፣ መስከረም 29 /2014 (ኢዜአ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስኮች ያስለጠናቸውን 6 ሺህ 556 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
ዩኒቨርሲቲው እያሰመረቃቸው ከሚገኙት መካከል 6 ሺህ 34 በመጀመሪያ ዲግሪ ፣517 በሁለተኛ ዲግሪ እና አምስት ተማሪዎች ደግሞ በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዛሬውን ሳይጨምር ቀደም ባሉት ዓመታት ከ63 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ተመልክቷል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ ዶክተር ሹመቴ ግዛው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና በኢትዮጵያ የኢንዶኔዢያ አምባሳደር አል ቡስይራ ባስኑር በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።