የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ በጭናክሰን ወረዳ የቆላ ስንዴ ልማትን ጎበኙ

76

ድሬዳዋ ፤ መስከረም 27/2014(ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጭናክሰን ወረዳ የለማን የቆላ ስንዴ ጎበኙ።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ  የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ በድጋሜ  ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪው የሆነው ጉብኝታቸው  በምስራቅ ሐረርጌ ዞን  ሌሎች  ወረዳዎችና ከተሞች የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ምረቃና የመሠረት ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል።

ከነዚህ መካከል በምስራቅ ሐረርጌ ባቢሌ ወረዳ ከ36 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የኢፋ ቦሩ ዋዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቆ አለገልግሎት ክፍት ሆነ።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የጨፌው  አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱርአህማን፣  የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን  በድሪ፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም