የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ

114

መስከረም 26/2014 (ኢዜአ)  ከትናንት በስትያ ምስረታውን ያካሄደው አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የቀረበለትን የካቢኔ አባላት ሹመት በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ።

 ከትናንት በስቲያ የምስረታ ጉባዔውን ያደረገው አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ልዩ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የቀረበለትን የሚኒስትሮች ሹመት በሁለት ተቃውሞና በ12 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ አባላቱ ሹመት የፖለቲካ አካታችነት፣ የትውልድ አካባቢ፣ ልምድ፣ ጾታ፣ ብቃት፣ የሃይማኖት ስብጥር፣ የማገልገል ፍላጎትን ማሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

አዲስ ተሿሚዎቹ ሌብነትን እንዲጸየፉ፣ አገርን በእኩልነት እንዲያገለግሉም አሳስበዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ።

በካቢኔ አባልነት የተሰየሙ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አባላትም ተቋም ሲመሩ ውጣ ውረዶች መኖራቸውን ተረድተው ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም አደራ ብለዋል።

የአዲሶቹ ሚኒስትሮች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-    

1. አቶ ደመቀ መኮንን ….….........ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

2. ዶክተር አብርሃም በላይ …..…....የመከላከያ ሚኒስትር

3. አቶ አህመድ ሽዴ ….…...........የገንዘብ ሚኒስትር

4. ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ……….የስራና ክህሎት ሚኒስትር

5. አቶ ዑመር ሁሴን ........…………የግብርና ሚኒስትር

6. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ………….የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር

7. ዶክተር ሐብታሙ ኢተፋ …………የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር

8. ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ……………….የትምህርት ሚኒስትር

9. ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ…………..የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር

10. አቶ ገብረመስቀል ጫላ ………….የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

11. አቶ መላኩ አለበል ……………….የኢንዱስትሪ ሚኒስትር

12. አቶ ብናልፍ አንዱዓለም…………የሠላም ሚኒስትር

13. ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ…….የፍትህ ሚኒስትር

14. ዶክተር ሊያ ታደሰ………………..የጤና ሚኒስትር

15. አቶ በለጠ ሞላ……………………..የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

16. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ……..….የቱሪዝም ሚኒስትር

17. አቶ ላቀ አያሌው …………………የገቢዎች ሚኒስትር

18. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ…………….…የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር

19. ኢንጂነር ታከለ ዑማ …………….የማዕድን ሚኒስትር

20. ዶክተር ፍጹም አሰፋ……………..የፕላን ልማት ሚኒስትር

21. ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ………….የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

22. አቶ ቀጀላ መርዳሳ………………..የባህልና ስፖርት ሚኒስትር

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም