ግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ገጽ(ፌስቡክ) የህፃናትን አዕምሮ የሚጎዱ ይዘቶችን እየተቆጣጠረ አይደለም

75

መስከረም 26/2014 (ኢዜአ) ግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ገጽ(ፌስቡክ) የህፃናትን አዕምሮ የሚጎዱ ይዘቶች ላይ በትኩረት እየሰራ አይደለም ሲሉ የቀድሞ ኩባንያው ሰራተኛ ፍራንቼስ ሀውገን ገለጹ።

ኩባንያው ህጻናትን የማይመጥኑ ይዘቶችን ከማስፋፋቱ በተጨማሪ በተጠቃሚዎች መካከል ክፍፍልን በማሰራጨት የዴሞክራሲ ስርዓትን እያዳከመ ነው ብለዋል።የቀድሞ የፌስቡክ ሠራተኛዋ የኩባንያው ጣቢያዎች እና መተግበሪዎች ልጆችን የሚጎዱ፣ክፍፍልን የሚያራምዱ እና የዴሞክራሲ ስርአት የሚያዳክሙ መሆናቸውን ለአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ተናግረዋል።

የ 37 ዓመቷ የቀድሞ የምርት ሥራ አስኪያጅ ፍራንቼስ ሀውገን በካፒቶል ሂል ችሎት ላይ ኩባንያውን በከፍተኛ ሁኔታ ነቅፈዋል።ጎጂ ይዘት ያላቸው መረጃዎች በመዋጋት፣ግልፅነትን በመመስረት ወደ ኢንዱስትሪ መር የምርምር መርሃ ግብር መፍጠር አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚያስፈልግ በመጠቆም።

"ሥራችንን እና ዓላማችንን በተሳሳተ መንገድ የሚገልጽ አካል ካለ ተቀባይነት የለውም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡በደብዳቤው ላይ በፌስቡክ ገጹ ላይ ለሕዝብ ይፋ ባደረገበት ወቅት የአዋቂዎችም ይሁን የህፃናት የአእምሮ ጤና ባሉ ጉዳዮች ላይ በጥልቅ "እንጨነቃለን” ብለዋል።ፌስቡክ በዓለም ላይ በጣም ተወዳጅ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ሲሆን በየወሩ 2.7 ቢሊዮን ንቁ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ይናገራል።

በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችም ዋትሳፕ እና ኢንስታግራምን ጨምሮ ሌሎች የኩባንያውን ምርቶች ይጠቀማሉ።ነገር ግን የተጠቃሚዎችን የግል ጉዳይ ከመጠበቅ ጀምሮ የተዛባ መረጃ መስፋፋትን ለመግታት በቂ ጥንቃቄ ባለማድረግ ወቀሳዎች እየደረሱበት ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም