የጂቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ አሸኛኘት ተደረገላቸው

74

መስከረም 25/ 2014 (ኢዜአ) የጂቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ በትናንትናው ዕለት በተካሄደው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ ታድመው ዛሬ ወደ አገራቸው አቅንተዋል።

በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለፕሬዝዳንቱ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

May be an image of 2 people, people standing and outdoors

በአሸኛኘት ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተሳትፈዋል።

በተያያዘም የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃን ሚኬል ሳማ ሉኮንዴ ትናንት ምሽት ወደ አገራቸው ሲያቀኑ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም