በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ-ሲመት ላይ የተገኙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላለፉ

131

መስከረም 24/2014 (ኢዜአ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ-ሲመት ላይ የተገኙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላለፉ።

መሪዎቹ የኢትዮጵያን በመንግሥት እና የነፃነት ተምሳሌት በመሆኗ ኢትዮጵያ ለመደገፍ ዝግጁ ነን ብለዋል።

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዓለ ሲመት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ  መሀመትን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ታድመዋል።

መሪዎቹ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የእንኳል ደስ ያላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም ኢትዮጵያን በመንግሥት እና በነፃነት ተምሳሌት እንዲሁም የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት ነች  ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካዊያን እናት በመሆኗ ሁላችንም ድጋፋችን አይለያትም ነው ያሉት።

የተረጋጋች፣ የበለፀገች፣ ሰላም የሰፈነባትና አብሮነት የነገሰባት ኢትዮጵያን እንሻለን ይህም እውን ይሆናል ሲሉ መሪዎቹ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም