የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አዲስ አበባ ገቡ

90

መስከረም 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ-ሲመት ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ፣ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባባል አድርገውላቸዋል።

May be an image of 4 people, people standing and outdoors

የ59 ዓመቱ ኡሁሩ ኬንያታ ከእ.አ.አ 2013 ጀምሮ ኬንያን በፕሬዚዳንት እየመሩ ይገኛል።

ኡሁሩ ኬንያታ ከእ.አ.አ 2008 እስከ 2013 የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩ ሲሆን የኬንያ የገንዘብ ሚኒስትርም ሆነው አገልግለዋል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፣ በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው የሚታወስ ነው።

ሁለቱ አገሮች በኢኮኖሚ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በማህበራዊ፣ በንግድና መሰረተ ልማት እንዲሁም በቀጠናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር እንደሚሰሩ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም