የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ አዲስ አበባ ገቡ

64

መስከረም 24/2014 (ኢዜአ) የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ በአዲሱ የመንግስት ምስረታ ስነ ሰርዓት ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ፣ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቲካን አያኖ አቀባባል አድርገውላቸዋል።

May be an image of 2 people, people standing and indoor

የ79 ዓመቱ ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ከእ.አ.አ ግንቦት 1999 ጀምሮ ጅቡቲን በፕሬዝዳንትነት እየመሩ ይገኛል።

ኢስማኤል ኦማር ጌሌ የጅቡቲ ገዢ ፓርቲ ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግራስ ፓርቲ መሪ ናቸው።

ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ እ.አ.አ በ2005፣ በ2011፣ በ2016 እና በ2021 በተደረጉ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎች ማሸነፋቸው ይታወቃል።

May be an image of 3 people, people standing, suit and text that says 'J2-HPV'

ፕሬዝዳንቱ በ2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር “ኢትዮጵያ በኔ ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት” ብለው ነበር።

ለኢትዮጵያ ያላቸውን ግላዊ ስሜት፣ በጂቡቲና በኢትዮጵያ መካከል ኢኮኖሚያዊ ውህደትን መፍጠር እንደሚገባ መናገራቸው ይታወሳል።

በዛሬው እለት ደግሞ በኢትዮጵያ አዲሱ የመንግስት ምስረታ ስነ ሰርዓት ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የኢፌዴሪ መንግስት ምስረታውን ዛሬ እያካሄደ ሲሆን ዶክተር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም