ህንድ በ2022 የህዋ ሳይንሰ ተመራማሪዎቿን ወደ ጠፈር ልትልክ ነው

83
ነሃሴ 9/2010 ህንድ እ.ኤ.አ በ2022 የህዋ ሳይንሰ ተመራማሪዎቿን ወደ ጠፈር እንደምትልክ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ይፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትርናሬንድራ ሞዲ ዛሬ በህንድ የነጻነት ቀን ባደረጉት የ80 ደቂቃ ንግግር “ህንድ በእውቅ ምርምራቸውና በፈጠራ ብቃት ግንባር ቀደም በሆኑት ሳይንቲስቶቿ ትኮራለች!” ሲሉም ተደምጠዋል። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው በ2022 የህዋ ሳይንስ ተመራማሪዎቿን ወደ ጠፈር እንደምትልክ ይፋ አደረጉ። የህንድ ባለሶስት ቀለም ሰንደቅ ዓላማ ጠፈር ላይ የሚያርፍበት የተመራማሪዎች ጉዞ  ከተቻለም ከ2022 ቀደም ብሎ ሊደረግ እንደሚችል ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቆሙት። ይህ ጉዞ ከተሳካም ህንድ አሜሪካ፣ ሩሲያ እና ቻይናን ተከትላ ተመራማሪዎቿን ወደ ጠፈር የላከች አራተኛዋ ሀገር ትሆናለች። ህንድ ሰው አልባ መንኮራኩር ወደ ማርስ በመላክ ከእስያ ሀገራት ቀዳሚዋ ናት። ምንጭ፦ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም