የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ካረን ባስ ጋር ተወያዩ

73

መስከረም 09 ቀን 2014 (ኢዜአ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ በጋራ በመሆን የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ከሆኑት ካረን ባስ ጋር ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላቱ ካረን ባስ እና ሳራ ጃኮፕስን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸው ይታወቃል።

በዛሬው እለት ደግሞ ከሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች ጋር ተወያይተዋል።

ካረን ባስ በኮንግረንሱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ስር የአፍሪካ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና ሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም የጥቁር አሜሪካውያን ኮንግረስ አባላት ጉባኤ ሰብሳቢም ናቸው።

ሳራ ጃኮፕስ ደግሞ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጣር ከ2020 ጀምሮ የኮንግረሱ አባል ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም