የአሸባሪውን ህወሃት የጥፋት ድርጊት ለአለም ለማሳወቅ በተጀመረው ዘመቻ ህዝቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደረግ ጥሪ ቀረበ

48

አሶሳ፤ መስከረም 05 / 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያን እውነተኛ መረጃ በመግለጽ የሽብርተኛውን ህወሃት ሀገር የማፍረስ የጥፋት ድርጊት ለሌላው ዓለም ለማሳወቅ በተጀመረው ዘመቻ ህዝቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደረግ ጥሪ ቀረበ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች የሚሳፉበት  “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ዘመቻ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

የክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን  ዘመቻውን   ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ሽብርተኛው ህወሃት ሃገር ለማፍረስ ጦርነት አውጆ ተግባራዊ ለማድረግ እየማሰነ ነው፡፡

የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን በማፍረስ ሴራ በተለይም በአሁኑ ወቅት የአማራ እና አፋር ክልሎች ህዝቦች ላይ  ጉዳት እየዳረሰ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በርካታ የዓለም መገናኛ ብዙሃን ይህንን እውነታውን በመተው እና የተዛባ መረጃ በማቅረብ ለማደናገር እየጣሩ  መሆኑን ገልጸው፤ የዘመቻው ዓላማም ይህንኑ የተዛባ መረጃ ማስተካከል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አንዳንድ  ምዕራባዊያን መንግስታትም ሆነ ህዝቡ አሁን ስለኢትዮጵያ ያለውን እውነታ  ከኢትዮጵያውያን እና ከመንግስታችን ብቻ በመረዳት ህግን የማስከበሩን ሂደት እንዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡

የ “ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት”ዘመቻ  የኢትዮጵያን እውነተኛ መረጃ በመግለጽ የሽብርተኛውን ህወሃት ሃገር የማፍረስ ሴራ ለሌላው ዓለም ለማሳወቅ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡
ሁሌም እውነትን ይዘው የሚታገሉት ኢትዮጵያውን በዚህኛውም ዘመቻ ውጤት እንደሚያመጡ እምነት አለኝ ብለዋል አቶ አሻድሊ ሃሰን ፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም የ “ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት”ዘመቻ መልዕክት ተቀብለው በመረዳት ተገቢውን ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም  አስታውቀዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  እስከ 100 ሺ የሚደርሱ ሰዎች “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ዘመቻ ለማሳተፍ ታቅዷል፡፡

ማንኛውም የክልሉ ነዋሪም  "እኔ ካልመራሁ ሃገር ትፍረስ" የሚለውን የሽብርተኛውን ህወሃት ድርጊት ለዓለም በማሳወቁ ሂደት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም